በቅርቡ በክልሉ ምክርቤት ጸድቆ ራሱን ችሎ እንዲቋቋም የተወሰነውን አዲሱን የጣና ተቋም መዋቅር (organizational structure) ለመቅረጽ ከባህርዳር ዩኒቨርሲቲ፤ ከአካባቢ ጥበቃ እና ከዓለም አቀፉ ጣናን መልሶ ማቋቋም ማህበር የተውጣጡ ምሁራን እየመከሩ ነው። መዋቅሩ የጣናን ስነምህዳር ሊንከባከብና ሊቆጣጠር በሚችል መልኩ ሳይንሳዊ አሰራርን የያዘ እንዲሆን በማድረግ ጣና የተጋረጠበትን ችግሮች በዘላቂነት መፍታት የሚያስችል እንደሚሆን ይጠበቃል።
(Photo Credit፤ ዶ/ር ይሁን ድሌ – የGCLTR የሳይንስ ቡድን መሪ – ከባህርዳር)