Date: July 15, 2022
Press release
ሶስተኛው የእንቦጭ ማጨጃ ማሽን ወደ ኢትዮጵያ ተላከ።
ኮቪድ ወረርሽኝን ተከትሎ በተከሰተው የፋብሪካዎች መዘጋት ምክንያት በጣም ተጓቶ
የነበረው ሶስተኛው የእንቦጭ ማጨጃ ማሽን መገጣጠም ተጠናቆ በቂ ፍተሻ ከተደረገለት
በኋላ ባለፈው ሳምንት ወደ ኢትዮጵያ ተልኳል። በኢትዮጵያ መርከቦች ድርጅት ትብብር
መሰረት በመርከብ ተጭኖ ወደ ጂቡቲ ወደብ ጉዞ ጀምሯል። በአምስት ሳምንት ውስጥ
ኢትዮጵያ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል። ማሽኑ ለአማራ ክልል መንግስት የጣናና ሌሎች ውሃ
አካላት ጥበቃና ልማት ኤጀንሲ በነጻ የተበረከተ ነው።
ይህ ማሽን ሶስተኛ ማሽን ነው – ክዚህ ቀደም ሁለት የእንቦጭ ማጨጃ ማሽኖ ለክልሉ
መለገሳችን ይታወሳል።
በአጠቃላይ ከ9 ሚሊየን ብር በላይ ($172,970 ዶላር) ወጭ የተደረገበት ይህ ባለ 80 የፈረስ
ጉልበት እንቦጭ ማጨጃ ማሽን በአንዴ 27.5 ኪዩቢክ ሜትር መያዝ የሚችል ሲሆን በጣና
ሃይቅ ላይ የተከሰተውን እንቦጭ ለማስወገድ በሚደረገው ርብርብ ላቅ ያለ ግልጋሎት
ይኖረዋል ተብሎ ይታመናል። ወጭው የተሸፈነው ከዚህ ቀደም በዋሽንግተን ዲሲ፤ በዳላስ፤
በችካጎና በእንግሊዝ ሃገር በተደረጉ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቶች ላይ ገንዘባቸውን በለገሱ
ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ነው። እንዲሁም ማሽኑን ከተመረተበት ካናዳ እስከ በመርከብ
እስከተጫነበት ወደብ (ባልቲሞር ወደብ) ድረስ ለማጓጓዝና ለወደብ ክፍያ ከማህበሩ በጀት
በላይ ወጭ በማስፈለጉ ይህንን ወጭ ለመክፈል ያገዛችሁን በካሊፎርኒያ የሚኖር አንድ
የጣና ወዳጅና የማህበራችን አመራር አባላት ምስጃናችን ከፍ ያለ ነው።
የኢትዮጵያ መርከቦች ድርጅት ያለክፍያ በነጻ ማሽኑን ከአሜሪካ እስከ ጂቡቲ ጭኖ
ስለወሰደልን ምስጋናችን ላቅ ያለ ነው። የአማራ ክልላዊ መንግስት ከጂቡቲ እስከ ባህርዳር
ያለውን የየብስ ትራንስፖርት እንደሚሽፍን ቃል ገብቷል።
በነበረው ከፍተኛ ውጣ ውረድ ብርታት ሆናችሁ ላበረታችሁን፤ ላመናችሁን፤ ለታገሳችሁን
ሁሉ ምስጋናችን ከፍ ያለ ነው። የማህበሩ አመራር አባላት የህዝብ ቃል ለመፈጸም ከሶስት
ዓመታት በላይ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትሉ ውጥኑን ዳር ለማድረስ በነጻ ጉልበታችሁን፤
ጊዜያችሁን እንዲሁም ገንዘባችሁን ሳትሳሱ ሰጥታችኋልና በመላው የጣና ወዳጆች ስም
እናመሰግናለን።
የክልሉ የጣና ሃይቅ ልማት ኤጀንሲ የትብብር ደብዳቤዎችን በመጻፍና ማሽኑ ከጉምሩክ
ቀረጥ-ነጻ እንዲገባ የሚያስፈልጉ ዶክሜንቶችን በማዘጋጀትና በማስፈጸም እገዛ
አድርጎልናልና ምስጋናችን ከፍ ያለ ነው።
ጤና ለጣና ይስጥልን! ዓለማቀፍ ትብብር ለጣና ደህንነት

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*