ዓለማቀፉ የጣና መልሶ ማቋቋም ማህበር (Global Coalition for Lake Tana Restoration) የገዛው ዘመናዊ የእንቦጭ ማጨጃ ማሽን ሚያዚያ አጋማሽ ላይ ኢትዮጵያ ይገባል
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++

በአትላንታና በእስራኤል ሃገር ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በተሰበሰበ በ67,290 የአሜሪካን ዶላር ከካናዳ የተገዛው አኳማሪን (Aquamarine H5-200) ዘመናዊ የእንቦጭ ማጨጃ ማሽን በኢትዮጵያ መርከብ እየተጓጓዘ ሲሆን ሚያዚያ አጋማሽ ላይ ኢትዮጵያ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል። የማሽኑን የውሃ ላይ ማጓጓዣ ክፍያ የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት በመሸፈን ለጣና ሃይቅ ያለውን አጋርነት በማሳየቱ እጅግ እናመሰግናለን። የኢትዮጵያ ጉምሩክ ባለስልጣን በበኩሉ ማሽኑ ከቀረጥ ነጻ እንዲገባ በመፍቀድ ለጣና ማህበረሰብ ያለውን አጋርነት አሳይቷል።

ዓለማቀፉ የጣና መልሶ ማቋቋም ማህበር ተጨማሪ ማጨጃ ማሽኖችን ለመግዛትና የሰውሃይል ስልጠና ለመስጠት እንዲሁም የተለያዩ ሃይቁን መልሶ ለማቋቋም የሚያግዙ አሰራሮችን ለመዘርጋትና ጥናቶችን ለማጥናት የሚውል በጀት ለመሰብሰብ በዋሽንግተን ዲሲ March 17 “ጤና ለጣና 2018″ በሚል መሪ ቃል ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም አዘጋጅቷል። በዚህ ዝግጅት ላይ ከ18 በላይ አርቲስቶች በመታደም ለጣና አጋርነታቸውን ያሳያሉ። በአንጋፋ ሰዓሊያን የተሳሉ ጣናን የሚያሳዩ የስዕል ስራዎች ለጨረታ ይቀርባሉ። ዝግጅቱ ከጣይቱ የባህል ማዕከልና ዒሻራ መልቲሚዲያ ጋር በትብብር የተዘጋጀ ነው።

ከስር የምትመለከቱት ፎቶዎቹ ማሽኑ ሲጫን የተነሱ ናቸው።

H5-200 Aquatic Harvester Commercial Invoice with details