04/21/2018
ከተጨማሪ ምርምርና ከብዙ የባለሙያዎች ምክክር በኋላ እነሆ ዘመናዊ ማሽን ($60,610) ከኮንቬዮር ($31,740 – እንቦጩን ከማሽን ተቀብሎ ወደ ሃይቁ ዳርቻ የሚያስተላልፍ መሳርያ ነው) ጋር ከነሙሉ መለዋወጫቸው በ 92,350 USD ከካናዳው ማሽን አምራች ግዥ ፈጽመናል። ይህም ሊሳካ የቻለው በዲሲው ፈንድሬይዚንግ ውጤት ነው! እንኳን ደስ አላችሁ! ተጨማሪ ማሽን ለመግዛት ደሞ ተጨማሪ የመስክ ጥናት ከባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ጋር እያደረግን እንገኛለን!
ከዚህ ቀደም የተላከው ማሽን በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ ጂቡቲ ወደብ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል!
በዲሲው ፈንድሬይዚንግ የተሳተፋችሁ በሙሉ ድካማችሁ ውጤት እነሆ!
ደረሰኞቹና ምስሎቹን ከታች ተመልከቱ።
Thank you for being part of this historical endeavor!
Global Coalition for Lake Tana Restoration